የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን የውኃ ስራዎች ኮርፖሬሽንን ጎበኙ”

የውኃ ስራዎች ኮርፖሬሽን (ውስኮ) የቀድሞዎቹን የአማራ ውኃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት እና የውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ ድርጅቶችን በውጤታማነት በመምራት ውስኮን ለአዲሱ ከፍታ ላበቁት የቀድሞ የቦርድ አመራሮች ምስጋናና እውቅና ሰጥቷል።

የውሃ ስራዎች ኮርፖሬሽን (ውስኮ) የቀድሞዎቹን የአማራ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት (አውስኮድ) እና የውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ ድርጅት (ውጉቁድ) አንጋፋ የልማት ተቋማትን በማዋሀድ በአብክመ መስተዳድር ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 207/2015 ዓ.ም ተቋቋመ ግዙፍ ኮርፖሬሽን ነው።

ኮርፖሬሽኑ በአማራ ክልልም ከክልሉም ውጪ የሚገነቡ የመስኖና ተፋሰስ፣ የግድብ እና የንጹህ መጠጥ ውኃ መሰረተ ልማት ግንባታ፣ የህንፃ ግንባታ በብቃት ማከንናወንን ጨምሮ፣ ለመጠጥ ዉኃና ለመስኖ አገልግሎት የሚዉሉ ጥልቅና መለስተኛ ጉድጓዶችን መቆፈር ፤ የውኃ መጠን ፍተሻና የውኃ ጥራት ትንተና መከወንና የኤሌክትሮ መካኒካል ስራዎች አቅርቦትና ተከላ የሚከውን ግዙፍና ገበያውንም የህዝብ ፍላጎትንም የሚመጥን ኮርፖሬሽን ሆኖ ነው የተደራጀው።

ያለውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ሀብት እንዲሁም ልምድ በማጣመር፤ በአደረጃጀት ፣ በአሠራርና በዘመናዊ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ከወቅቱና ካለዉ የገበያ ፍላጎት አንጻር ራሱን ይበልጥ በማደራጀት እና የመፈጸም አቅሙን በማሳደግ በውኃ ልማት ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ በመሆን እንዲሰራም የተደራጀ ነው።

በተቋቋመ በመጀመሪያው ዓመት በመጀመሪያወዎቹ 9 ወራት በርካታ ውጫዊና ውስጣዊ ችግሮችን በመቋቋም ተስፋ የሚጣልበት አፈፃፀም አመዝግቧል።

“የውኃ ስራዎች ኮርፖሬሽን አንጋፋዎችን የአማራ ክልል የውኃ ስራ የልማት ድርጅቶች በማዋሃድ የተጠናከረ፣ በዘርፉ ክልሉ ያለበትን የቤት ስራዎች ለመወጣት ወደ ገበያው የገባና የውኃ ዘመናዊ አደረጃጀትን ከቴክኖሎጂ ጋር የተላበሰ ተቋም ነው!!” ሲሉ የውስኮ የቦርድ ሰብሳቢና የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን ገልጸዋል።

“እየተሻሻለ ያለውን የክልሉ ሰላም በምቹ አጋጣሚነት በመውሰድ ስራዎቹን በመላ ክልሉ ከማስፋት በተጨማሪ፣ አዲስ አበባን ጨምሮ በሌሎች ክልሎችም የልማት ተምሳሌትነቱን በውጤታማነት ለማሳየት በበለጠ መስራት ይጠበቅበታል::” ሲሉም ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ የቀድሞዎቹን አውስኮድ እና የውኃ ጉድጓድ ቁፈሮ ድርጅቶች በተለያየ ጊዜ በውጤታማነትና በስትራቴጅክ አመራር ለመሩ እንዲሁም ወደ ኮርፖሬሽን ደረጃ እንዲያድግ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የቀድሞ የቦርድ አመራር አባላትን በባሕር ዳር ከተማ የምስጋናና የእውቅና ስርዓት ሰጥቷል።*

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top