ማማሩ አያሌው (ዶ/ር) የአብክመ ውኃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
በድርቅ ተጎዱ የኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር አካባቢዎች አስቸኳይ የውኃ አቅርቦትና ለችግሩ ምላሽ የውኃ ተቋማትን አቅም ለማሳደግ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ድጋፎች ተደርገዋል።
====================================
የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮ በድርቅ ለተጎዱ የአማራ ክልል አካባቢዎች የሚያደርገውን የውኃ አቅርቦትና የመጠጥ ውኃ ተቋማትን ለችግሩ በቂ ምላሽ እንዲሰጡ አቅማቸውም የሙያጠናክሩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አጠናክሮ ቀጥሏል።
የአማራ ክልል ውኃና ኢነርጂ ቢሮና አጋር ድርጅቶች ባለፉት ወራት በሰሜን ጎንደር፣ በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች እንዲሁም በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረሳችን ይታወሳል።
በዞኖቹ የተደረገው ድጋፍ የመጠጥ ውኃ ተቋማትን የመጠገንና አቅማቸውን የማጎልበት፣ የውኃ ጉድጓዶች ውኃ የማመንጨት አቅም በተዳከመባቸውና ከውኃ ተቋማት ለራቁ አካባቢዎች ደግሞ በቦቴ ውኃ የማቅረብና የውኃ አቅርቦትና የንጽህና አጠባበቅ ቁሳቁሶች ድጋፍ ተደርጓል።
የአሁኑና 4ኛው ዙር ድጋፍ በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች ነው። ድጋፉን ለብሄረሰብ አስተዳደሩ ውኃና ኢነርጂ መምሪያ ማድረስ ተችሏል፣ ቢሮው ሁሌም እንደሚያደርገው ሁሉ ከዞኖች ጋር በቅርበት በመስራት ችግሩ ባለባቸው ቀጣናዎች ተጨማሪ ድጋፍ ማድረጉን የሚቀጥል ይሆናል።
የድርቅ አደጋ ምላሽ ድጋፉ በአስተዳደሩ ባቲ ወረዳ የተደረገ ነው። ቢሮው ከዚህ በተጨማሪም ከውኃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በብሄረሰብ አስተዳደሩ የተገነቡትን የኢዶ መድኔኔና ጋሬሮ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ወደ አገልግሎት ለማስገባት የ4 ፓምፖች ድጋፍ አድርጓል።
ለብሄረሰብ አስተዳደሩ በቢሮው በሚኒስቴሩና በአጋር ድርጅቶች ትብብር የተደረገው ድጋፍ አጠቃላይ የገንዘብ መጠን ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ ነው።