የህዝባችን የዘመናት ጥያቄ የሆነዉ ታላቅ ድልድይ በታላቁ የአባይ ወንዝ እውን ሆኗል።

በውቢቷ ባህርዳር ከተማ ተንጣሎ በሚገኘው ታላቁ የአባይ ወንዝ ላይ ያለው እና ከ60 ዓመታት በላይ የአገልግሎት ጊዜን ያስቆጠረው ድልድይ እድሜ ጠገብ ከመሆኑም በላይ ዘመኑን የዋጀ ፈጣንና ተደራሽ የሆነ የህዝብ ትራንስፖርት በመስጠት በኩል ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት መጨናነቅን ሲፈጥር ቆይቷል።

በዚህም ምክንያት የባህርዳር እና አካባቢውን ህዝብ ጨምሮ በሌሎች የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ተጓዦች ላይ ሲፈጥር በነበረው ጫና የተለዋጭ ድልድይ የይገንባልን ጥያቄ ለበርካታ ዓመታት ሲነሳ ቆይቶና የግንባታው ሄደት በሚገባ ከተከናወነ በኋላ እንሆ በዚህ ወቅት ሙሉ አገልግሎት መስጠት በሚያስችል ቁመና ላይ ደርሷል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top