የከተማውን የውሃ መገኛ ቦታዎች በጥናት ላይ ተመስርቶ ዘላቂ የቀጣይነት መፍትሄ መስጠት እንደሚገባ ተገለጸ.

የደብረብርሃን ከተማ የውሃ መገኛ ቦታዎችን ከብክለት ቀድሞ ለመከላከል ከአጋር አካላት ጋር ውይይት ተካሄደ

በውይይቱም የማህበረሰብ ተወካዮች፣የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ የዘርፉ ምሁራን፣ የክልሉ የውሃ ባለሙያ፣ የደብረብርሃን ከተማና የሰሜን ሸዋ ዞን የሚመለከታቸው ተቋማት የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣የውሃ አገልግሎት ጽህፈት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

ለውይይት መነሻ የዘርፉ ምሁራንና የተቋማት ኃላፊዎች ጥናታዊ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተደርጎበታል።

የደብረብርሃን ከተማ ውሃ አገልግሎት ጽህፈት ቤት መሠረት መንገሻ እንደገለጹት ሰፋፊ የውሃ መገኛ ቦታዎች መጠናታቸውን አንስተዋል። ከብክለት እንዲጠበቁ ሁሉም ኃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የደብረብርሃን ከተማ ከንቲባና የውሃ ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ በድሉ ውብሸት ውይይቱን ሲያጠቃልሉ እንደገለጹት ልማት በፕላን እንደሚመራ ጠቅሰው በደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ እየተዘጋጀ የሚገኘው አዲሱ መዋቅራዊ ፕላን የከተማውን የውሃ ብክለት ችግር በዘላቂነት መፍትሄ ሊሰጠው እንደሚችል አመልክተዋል፡፡

ከሪል ስቴት ጋር ተያይዞ ለተነሳው ችግር በዘርፉ ባለሙያዎች በሚቀርበው የጥናት ግኝት መሠረት ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጠው መግባባት ላይ መደረሱን አስረድተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት በአጭር ጊዜ ቴክኒካል ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ እንደሚገባና በግኝቱ መሠረት ተፈፃሚ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top